የመሪጌታ ልሳነወርቅ ምስክርነት
- Emishaw Tekola

- Feb 19, 2025
- 1 min read
Updated: Feb 21, 2025
መሪጌታ ልሳነወርቅ ካሳበል፤ ይባላል እንደነገረን ከሆነ የተወለደው በወሎ ላሊበላ አውራጃ ነው በቤተ ክህነት የትምህርት እርከን እስከ መሪጌታ ነት ደረጃ የተማረ በእምነቱም የተወደደ ጥሩ መምህር እንደነበር ይናገራል

መሪጌታ ልሳነወርቅ ታሪኩ ረጅም ቢሆንም በአጭሩ እንዲህ ነው፤ ይህ ወጣት በአስገራሚ ጥሪ የወንጌል ምስክርነት ሰምቶ ጌታን ካገኘባት ሰዓት አንስቶ እዚያው በሚያገለግልበት ደብር ወንጌልን በድፍረት ሲመሰክርና ሲያስተምር የሰሙ የእምነቱ ተከታዮች በተለያየ ጊዜ ባስነሱበት ስደት የያዘውን የወንጌል ዕውነት አልለቅም በማለቱ ምክንያት በጥቂት ሰዎች አሳዳሚነት እጅና እግሩን አስረው ከረጅም የገደል አፋፍ ላይ ወርውረውት ከ2ቀን በኋላ በፍለጋ በህይወት እንደተገኘ ነግሮናል ይህ ሰው ከዚያ በኋላ ነበር በኮሪያ ሆስፒታል ህክምና ሲከታተል ቆይቶ ከፍተኛ የነርቭና የአጥንት ስብራት በማጋጠሙ በሃገር ውስጥ ከዚህ በላይ መርዳት ስላልተቻለ በጀርመን ሃገር በሚገኝ ከፍተኛ ሆስፒታል እንዲታከም ሪፈር የተደረገው መሪጌታ ልሳነወርቅ ላለፉት ለ10 ዓመታት ያህል ከወገቡ በታች መንቀሳቀስ ተስኖት በአልጋላይ ቆይታው ወቅት ሌላ የገጠመው ችግር የልብ ህመም ነበር ለዚህም ከፍተኛ ህክምና አድርጎ በየወሩ ለሚወስዳቸው መድሃኒቶች እስከ 5000(5ሺ) ብር ድረስ እንደሚያወጣ ነግሮናል፡፡ ምንም ህመሙ ቢደራረብበትም እስካሁን በእምነቱ ጠንካራ ከህመሙ ማየልና ከባለቤቱ ና ልጆቹ መሰቃየት የተነሳ አምላኩ እንዲወስደው ከመለመን ውጪ አንድም ቀን እንኳ ለምን ብሎ አማርሮ እንደማያውቅ አጫውቶናል፡፡
የ14 ዓመት የትዳር አጋሩና የልጆቹ እናት ከሆነችው ወ/ሮ ጥሩነሽ ደምሌ የ10 ዓመት ወንድ ልጅና የ8ዓመት ሴት ልጅ አፍርቷል ባለቤቱ መንፈሰ ጠንካራና ባላት አቅም የቀን ሥራ እየሰራች የታመመው ባለቤቷንና ልጆችዋን ተሸክማ ትኖራለች በአሁን ሰዓት ለ4 ዓመታት በአንድ በጎ አድራጊ ሰው በነጻ እንዲኖሩበት ከተሰጣቸው ቤት በቅርብ ሊለቁ የተጠየቁና ለጊዜው ብቻ እዚህ እንደሚኖሩ ወደፊት ደግሞ እግዚአብሔር ማረፊያ እንዲያዘጋጅላቸው በጸሎት እንድናግዛቸው ጠይቀውን ተለያይተናል፡፡
ከሁለት ወራት በፊት ከተለያዩ አቅጣጫዎች በተገኙ እርዳታዎች ለህክምና ወደህንድ አገር ሄዶ በመታከም ላይ ይገኛል
ከልሳነዎርክ ጋር በየሳምንቱ ሐሙስ በስልክ የምንገናኝ ሲሆን በህክምና አሁን የደረሰበትን ሁኔታ ማወቅ ቢፈልጉ በድህረ ገጻችን ላይ ገብተው መመልከት ይችላሉ Support Us | dffay.org
Comments